Home

Slider
Message from the Director

Ato Getachew Mengiste-Director General
News and Updates

 Ethiopian Civil Aviation Authority organized a Workshop under the mantra ” The Acceleration of the single Air Tansoprt Market (SAATM) Ethiopian Stakeholders Roadshow” in coalition with African Civil Aviation Commission ( AFCAC) from May 10-11,2023 at SkyLight Hotel. Excerpts in picture.

 የህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 12ኛ ዓመት አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ሰራተኞችና የማኔጅመንት አባላት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን 12ኛ ዓመት በማስመልከት ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የግማሽ ቀን የውይይት መድረክ አካሄዱ፡፡ ከውይይቱ ቀደም ብሎ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አስተባባሪ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት የተዘጋጀ የማወያያ ሰነድ በተቋሙ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የቀረበ ሲሆን የቀረበውን ፅሁፍ በመንተራስ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡ ውይይቱን የመሩት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኤርናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ንጉሴ ናቸው፡፡

 ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ሠራተኞች ጋር ተወያዩ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ሠራተኞች ጋር በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ/ም ተወያዩ፡፡ ዶ/ር ዓለሙ ስሜ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስራ ጉብኝት ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው ቢሆንም ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮች ጋር ግን በተለያዩ መድረኮች በጋራ ሲመክሩ ቆይተዋል፡፡ በዛሬው ዕለትም ለግማሽ ቀን በተደረገው ውይይት በዋናነት ‘የመተዋወቂያ መድረክ ነው’ ያሉት ዶ/ር ዓለሙ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እየገጠሙት ባሉት ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ላይ በጋራ መክረዋል፡፡ ከሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም ሚንስትሩ ሠፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከውይይቱ ቀደም ብሎ በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ በአቶ መንግስቱ ንጉሴ የኤርናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የጥናት ፅሁፍ ቀርቧል፡፡

 ብሔራዊ የፈልጎ ማዳን ኮሚቴ ሊቋቋም ነው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የመንገደኞች አውሮፕላን አደጋ ቢከሰት ለአደጋ የተጋለጡ ሰዎችንና አፋጣኝ እርዳታ የሚፈልጉ የመንገደኞችን ህይወት ለመታደግ የሚያስችል የፈልጎ ማዳን ኮሚቴ ለማቋቋም ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም የመጀመሪያውን ውይይት አካሄደ፡፡ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ ሰብሳቢነት በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የግማሽ ቀን ውይይት ከኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ከመከላከያ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስቴር ፣ የግል የአየር በረራ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ኃላፊዎች እና ሌሎች ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በቀጣይ ስብሰባ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የተዋቀረ ሀገራዊ የፈልጎ ማዳን ኮሚቴ (National Search and Rescue Committee) ለማቋቋም ተስማምተዋል፡፡ በዕለቱ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ዳይሬክተር አቶ ዮሀንስ አበራ አለም አቀፍ የፈልጎ ማዳን አሰራሮችንና ድንጋጌዎችን ከሀገራችን ነባር ልምዶች ጋር በማነፃፀር ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የቀረበውን ገለፃ በመንተራስ በርካታ ዝርዝር ርዕሰ ጉዳዮች ተዳሰዋል፡፡ በቀጣይ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚዋቀረው ይህ ብሔራዊ የፈልጎ ማዳን ኮሚቴ ሀገራዊ እቅድ እንደሚያዘጋጅ የሚጠበቅ ሲሆን እቅዱ የፖሊስ አካላትን እና በክልል ደረጃ ያሉ መሰል ተቋማትንም ማካተት ሰፋ በስፋት እንደሚሰራበት የተገለፀ ሲሆን በተለይም በፈልጎ ማዳን ተግባሩ ላይ ጥቆማ በመስጠትና የተጎጂዎችን ህይወት በመታደግ እስከዛሬም ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ የነበሩ የሀገራችን ገበሬዎችና ባጠቃላይ የህብረተሰብ አካላት እንደመሆናቸው ይህ የፈልጎ ማዳን ተግባር እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚያስፈልግ ተሰብሳቢዎቹ ተናግረዋል፡፡ ሁልጊዜም አለም አቀፍ ድንጋጌዎችን መሰረት አድርጎ ተቋማዊ ህጎችንና ስታንዳርዶችን አዘጋጅቶ ስራዎችን የሚያከናውነው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በአዋጅ ከተሰጠው ኃላፊነቶች አንዱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የፈልጎ ማዳን ኮሚቴ በማቋቋም የሌሎች መንግስታዊ ተቋማትን ገንዘብና አቅምን ጭምር በማስተባበር ይህን ሀገራዊ ኃላፊነት መወጣት መሆኑ ይታወቃል፡፡ አዲስ የሚቋቋመው ኮሚቴ ከዚህ ቀደም ለበርካታ አመታት ሲንቀሳቀስ የነበረውን ኮሚቴ በመተካት የሚቋቋም ሲሆን ወቅቱን ያማከሉ በድሮን የተደገፉ የፈልጎ ማዳን ስራዎችን የመሳሰሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ መሳሪያዎችንና አሰራሮችን ለመተግበር ስትራቴጂክ እቅድ ቀርፆ መስራት እንደሚያስፈልግ ተነስቶ ከዚህ ቀደም ከነበሩ ልምዶች በመነሳት ክፍተቶችን በማረም በተሻለ አደረጃጀት እንደሚንቀሳቀስ ይጠበቃል፡፡

 ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ካውንስል አባል በመሆን በከፍተኛ ድምፅ ተመረጠች!!
ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ካውንስል አባል በመሆን በከፍተኛ ድምፅ ተመረጠች!! የአለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) በካናዳ ሞንትሪያል ከተማ እያካሄደ ባለው 41ኛው ጉባኤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድምፅ ካገኙ ሀገራት ተርታ በመሰለፍ የድርጅቱ ካውንስል አባል ሀገር ሆና ተመረጠች፡፡ ለካውንስሉ አባልነት ከአፍሪካ ከተመረጡት ጥቂት ሀገራት መሀከል ኢትዮጵያ በከፍተኛ ድምፅ የተመረጠች ሲሆን ስምና ዝና ያላቸው እንደ ጋና ያሉ ትላልቅ ሀገራትን በመብለጥ ነበር በከፍተኛ ድምፅ የተመረጠችው፡፡ በአጠቃላይ በአለም ላይ በአቪዬሽን ዘርፍ ከፍተኛ ስምና ዝናን ያተረፉ 36 ሀገራት አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በትናንት ዕለት ማለትም መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በሶስት ክፍል በተካሄደው ምርጫ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ውድድር ሶስተኛው ሲሆን ድምፅ ከሰጡ 175 ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ 154 ድምፅ በማግኘት በምድቧ ከተካሄደው ውድድር ኳታርን በመከተል ሁለተኛውን ትልቁን ድምፅ አግኝታለች፡፡ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በአቪዬሽን ደህንነት ከሁለት አመታት በፊት በአለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) safety oversight ምዘና 88.59 ነጥብ በማምጣት እጅግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ የሚታወስ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን በአቪዬሽን ደህንነት በከፍተኛ ማማ ላይ እንዳስቀመጣት ይታወሳል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ሀገራችን ባስመዘገበችው ውጤት መላው ኢትዮጵያዊያንን እንኳን ደስ አላችሁ ሲል ደስታውን ይገልፃል!!!! አጠቃላይ የካውንስሉን ጉባኤና ሀገራችን ባስመዘገበችው ውጤት ዙሪያ የልዑካን ቡድኑ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥበት መሆኑን ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

 Information on Ethiopian Flight Information Region (FIR)!!
Ethiopian Civil Aviation Authority would like to state that any flight in Ethiopian Airspace including Addis Ababa international airport is safe and secured. The warning issued and released by media outlets is baseless and quite contradictory to the reality. We strongly assure users of our airspace and airports that we are not compromising their safety and security as we are taking every measure to ensure safe and secured flight operation as before; we are complying with the international standards of safety and security measure

 Ethiopian civil aviation Authority – Statement NOV.5/2020
On the fourth of November 2020 Ethiopia, civil aviation has notified the closer of the international and domestic flying routes which crosses Ethiopian northern air space and notified all states through NOTAM (Notice to Airmen). In addition to this, we would like to announce that the air space of the Tigray region is closed for any flight; accordingly no flight is expected violation of this notification. Read more…

 First ever self-prepared FPD Training Kicks off!
Ethiopian Civil Aviation Authority (ECAA) started to provide ‘Flight Procedural Design Training’ (FPD) to its employees today, the first self-designed and prepared type of training ever provided in Africa. The training, which will be supported by practical sessions, would enable trainees to design new Air Routes for the air transport service. Read more…


 የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር በዘርፉ የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ላይ ዉይይት ማድረግ ጀመረ።
ዉይይቱ እየተካሄደ ያለዉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የተጠሪ ተቋማት ሃላፊዎች በተሳተፉበት ሲሆን ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ የተግባር አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ በዝርዝር በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ አንስተዋል። Read more…


 የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሰው አልባ አይሮፕላን አጠቃቀም መመሪያ አዘጋጀ
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት አንዱ የሆነውን የሀገሪቱን የአየር ክልል የመቆጣጠርና ደህንነቱ የተጠበቀና ምቹ የአየር ትራንስፖርት አቅርቦት እንዲኖር ማረጋገጥ ሲሆን በሀገራችን እያደገ የመጣውን የሰው አልባ አይሮፕላን (ድሮን) አጠቃቀምን የሚመለከት መመሪያ አዘጋጅቷ፡፡ Read more…


 ECAA devises circulars to mitigate the impact of Covid-19 in the industry
2019 marks the 75th The Ethiopian Civil Aviation Authority (ECAA) devised five circulars bidding to curtail the colossal impact of the global pandemic, Covid-19, in the industry; thereby ensuring the utmost satisfaction of customers. Read more…


 የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል ስራውን ለማሳለጥ የሚረዱ ሰርኩላሎችን አዘጋጀ
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በመላው አለም የተከሰተውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ የካርጎ አገልግሎት አሰጣጥ ደህንነት፣ አይሮፕላኖችን በኬሚካል ርጭት ከቫይረሱ ንክኪ ነፃ ለማድረግ፣ Read more…


ECAA የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከአፍሪካ ከፍተኛውን አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከአፍሪካ ከፍተኛውን አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ ለአንድ ሳምንት በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የተለያዩ የስራ ክፍሎችን ኦዲት ሲደርግ የቆየው የአለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የልኡካን ቡድኑ ሪፖርቱን አቀረበ፡፡ Read more…

>>Read more news…

Quick Links
Voluntary Hazard Reporting Form
Press Release
RPAS Draft Regulation Validated
Events
Announcements
  Information on Ethiopian Flight Information Region (FIR)!!
  የሰው አልባ አውሮፕላን (Drone) ማስታወቂያ
  የሰው አልባ አውሮፕላን(ድሮን) ምዝገባ
NoAgencyContactTel.:Fax:E-mail Address
1Zebra AviationMr. Afework Yohannes+251911426909 zebraaviation@gmail.com
2Dream Aviation SupportMr.Taye Gemechu +251911419753 /+251975380340support@ethiodreamaviation.com
3AMBL Facilitation & LogisticsMr. Mekonnen Hunegnaw +251911500016mekonnenhunegnaw@gmail.com
4Aquarius AviationMrs.Freheywot Tessema +251116624343 +251116624373fre@aquarius-ethiopia.com
5Abyssinian Flight ServiceCpt.Amare G/Hanna +251116620623+251116620620 dmd@abyssinianflights.com
6National AirwaysCpt.Abera Lemi +251911201722 operations@nationalairways.com
7Zemen Flying ServiceMr.Eshetu Astatkie +251911679218 info@flyzemen.com
8TSK Aviation & LogisticsMr.Kassahun Kena +251910064631kass@tskaviation.com
9Runway Flight SupportMr.Amare G/Yohannes +251911518181runwayethiopia@gmail.com
10Krimson Aviation ConsultingMr.Dawit Lemma +251912618266dawit@krimson.aero
11Nor AviationMr.Feseha Kiros+251929333990
12International Cargo & Aviation ServicesMr.Fetehanegest Kindeya +251115524747+251116611547
13Cockpit Aviation & Flight Support Mr.Gelawdewos H/Selassie +2519524730878maru731@gmail.com
14Canal Aviation & LogisticsMrs.Yeshimebet Tilahun +251116154678yeshimebet.tilahun@gmail.com
Selected Information
Selected Services
Related Links